Quantcast
Channel: Oromo Videos & News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1719

Another Opposition Party Says ‘No’ to the Master Plan & Govt’s Violence Against Oromo Protesters

$
0
0

The following is a statement of the ‘Gadaa System Advancement Party,’ one of the opposition groups operating in Ethiopia. The statement is in Afan Oromo and Amharic (the Amharic version is posted below).

GadaaParty20152

ፊንፊኔ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተነደፈውን ማስተር ፕላንና የኦሮሚያ ከተሞች ማሻሻያ ሕግን በመቃወም ከገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ /ገዳ/ የተሠጠ መግለጫ

የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ስም ለዘመናት መስዋህትነት የሚከፍለው ከሌሎች ጋር አብሮ ለመኖር ነው፡፡

የሕወሃት መሪዎች የፌዴራል ሥርዓትና የአገሪቱ ሕገ-መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ የመከላከያን፣ የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በመቆጣጠር ሳይንቲስቶችና የዓለም ጀግኖች የሚፈልቁበትን የኦሮሞ ሕዝብን በመናቅ “ለልማታችሁ እኛ እናውቅላቸዋለን” በማለት የወቅቱ ደካማ የኦሮሚያ አስተዳደርን ተጠቅሞ በኦሮሞ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በማግባት ፊንፊኔን ወደ ኦሮሚያ ለማስፋፋት እና ቁልፍ የሆኑ ከተሞችን ከኦሮሚያ ለመለየት በያዙት ግትር አቋም የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞታል፡፡ የተማረ ሕዝብ መብቱን ስለሚጠይቅ ተማሪዎቻችን መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ ደብተርና እስክሪፕቶ እንደያዙ በጭካኔ ተገድለዋል፡፡ የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በጥቅምት ወር 2008 ባደረገው ስብሰባ በማስተር ፕላኑ ምክንያት አንድም የኦሮሞ ተማሪ እንዳይሞት በጋራ ተስማምተን እያለ የተማሪዎቻችን የጭካኔ ግድያ ድብደባና እስራት መቀጠሉ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ይህ የተማሪዎች ግዲያ የሕጻናት መብት ኮንቬንሽን ከመጣስ አልፎ የሕዝብ ቁጣ ከመቀስቀስ ከድርቁና ከረሃቡ ጋር ተጨምሮ አገሪቱን ወደ ውድቀት እንዲትሄድ ያደርጋታል፡፡ ስለሆነም፡-

1. በኦሮሚያ ውስጥ እየተፈጸመ የሚገኘው የጭካኔ ግድያ ድብደባና እስራት ካልቆመ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ስጋት ፈጥሮ ነገ ልጆቻችን አብሮ ለመኖር ስለማይችሉ ግድያው በአስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲደረግ፤ የሕዝብ ጥያቄን መመለስ አቅቶት የፖለቲካ ኪሳራ እየደረሰ የሚገኘው ኦሕዴድም ዋና አለቃው የኦሮሞ ሕዝብ መሆኑን አውቆ የታሪክ ተጠያቅ ከመሆን ኃላፊነቱን እንዲወጣ፤

2. ሕገ-መንግስቱና የፌዴራል ሥርዓት ከሚፈቅደው ወጪ ፊንፊኔን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት ተጨባጩ ማስረጃ የፊንፊኔ ቀበሌዎች ወደ ወረዳ እንዲያድጉና ከሌላ ክልሎች መጥተው በነዋሪዎች እንዲጨናነቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኦሮሞ አርሶ አደሮችን አፈናቅሎ እንዲገነቡ መደረጉና የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 49(5) ተግባራዊ አለመደረጉ ነው፡፡ ስለሆነም ፊንፊኔ ወደ ጎን ተለጥጣ ኦሮሚያን በምስራቅና በምዕራብ ለመለያየት የተነደፈው ማስተር ፕላን እንዲሰረዝና ማስተር ፕላኑን ለማስተባበር የተቋቋመው ጽ/ቤትም እንዲዘጋ፤

3. ለአንድ ፌዴራል መንግስት ቁልፍ መ/ቤቶች የሆኑት የመከላከያን የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር መዋሉ አገሪቱን ወደ አለመረጋገትና መለያየት ስለሚወስድ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 39(3) መሠረት እነዚህን ቁልፍ የአገሪቱ ስልጣን ለሕዝብ ተመራጮች እንዲሰጥ እንጠይቃለን፤

4. የኦሮሞ ሕዝብ አንድነቱና የሀገሩ ባለቤትነት መብት አጥቶ በየጊዜው ለከፋ አደጋ ሊጋለጥ የቻለው ዋና ምክንያት ዴሞክራሲው የገዳ ሥርዓቱ ስለፈረሰበት ነው፡፡ ስለሆነም ያልተደራጀ ሕዝብ ለድል እንደማይበቃ በመገንዘብ የገዳ ሥርዓት አስተዳደርን ለመመለስ በጽናት እየታገለ በሚገኘው በገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ (ገዳ) ስር ተደራጅታችሁ የሕዝባችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች እንዲመለስ በሰላማዊ መንገድ በጋራ ለመታገል ከጎናችን እንዲትቆሙ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሁሉም የአፍሪካ ብሔሮች መብት ከተከበረ: አንድ የአፍሪካውያን ፌዴራላዊ መንግስት መመስረት ይቻላል!

ፍትህ ለኦሮሞ ሕዝብ! / Justice for Oromo People! / SIRNA GADAA KEENYAAN BULLA!

ታህሳስ 2 ቀን 2008 ዓ.ም.
ፊንፊኔ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1719

Trending Articles